Breaking News🇪🇹

#BREAKINGNEWS🇪🇹

Namoonni nageenya biyyaarratti sodaa uumaniifi karaa sharafa alaa biyya dhabsiisuun yakka waliin dhawuu teelekoomiin shakkaman 30fi meeshaaleen gara garaa to’ataman.
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Namoonni dhuunfaa nageenya biyyaarratti sodaa uumaniifi karaa sharafa alaa biyya dhabsiisuun yakka waliin dhawuu teelekoomiin, shakkaman 30fi meeshaaleen gara garaa to’atamaniiru.

Magaalota Finfinnee, Shaggar, Bishooftuu, Adaamaa, Hawaasaafi Jimmaatti hojii qindoominaan hojjetameen keessattuu meeshaalee telekoomii ittiin waliin dhahaniifi shakkamtoonni 30’nni harkaafi harkatti qabamuun to’atamuun ibsameera.

Bulchiinsi Odeeffannoo Nageenyaa, tajaajila odeeffannoofi nageenya biyyaalessaa Poolisii Federaalaa Itiyoophiyaa waliin qindoomuun ji’oottan sadan darban h namoota hojii waliin dhawuu teelekoomirratti bobba’an irratti iccitiin hordoffii cimaa taasisaa turuu ibsa waloon miidiyaaf erganiin beeksisaniiru.

Shakkamtoonni kunneenis manneen namoota dhuunfaa kireeffachuun meeshaalee ittiin waliin dhahaniin hojjetaa turuu ibsichaan eerameera.

Siimi kaardonni Itiyoo teelekoomiifi Safaariikoom hojii seeraan alaa kanaaf dhimmi itti bahamaa ture kumni 200 ol to’atamaniiru.
Kana malees meeshaalee to’ataman keessatti Meeshaan al tokkootti siim kaardii 121 waliin dhawuu danda’u akka qabame ibsameera.
Meeshaalee kanneenitti dhimma bahuun hojii waliin dhawuu kanaan Tajaajila Teelekoomii idil Addunyaarraa sharafa Itiyoophiyaan argachuu maltu dhabsiisuun ibsichaan eerameera.

Sababa kanaan ji’oota jahan darbanitti qofa Itiyoo Teelekoom birrii miiliyoona 500 ol dhabuun ibsameera. 

 Meeshaaleen kunneenis karaa seeraan alaan gara Itiyoophiyaa akka galfaman eerameera.

Gochiifi meeshaaleen kunneen beekumsa Itiyoo Teelekoomiifi Safaariikoomiin ala bilbiloota biyyoota alaarraa bilbilaman neetworkii mataa isaa uummateen maamiltootaaf kan dhiheessu ta’uun himameera.  

Gochi kun sodaa biyyaa ta’uu bira darbuun maamiltoonni sirnaan tajaajila bilbilaa akka hin fayyadamneef toora dhiphisuun komii uummataa babal’iseera. 

Yakka waliin dhawuu kana keessatti namoonni hirmaatan kunneen qooda fudhattoota biyyoota alaatii hanga namoota mana isaanii kireessaniitti harka wal keessaa akka qaban ibsameera.

Faddaaltonni siimkaardiifi kaardii mobaayilaa dhaabbilee lachuu, daangaarraa hanga giddu galeessaatti jara kana waliin qindoomuun deddeebisaniis akka jiran beekameera.

Keessattuu lammilee Keeniyaa, Somaaliyaafi biyyoota biroo teessoosaanii taasifatan waliin ta’uun hojii kanaaf qaxaramuun kanneen hojjetaa turanis akka jiran irra gahamuun ibsameera. 

Dhaabbileen nageenyaa kunneenis hojiilee gama kanaan eegalaman cimsanii akka itti fufan eeraniiru.

Uummannis gochoota akkasii yoo argee shakke saaxiluurratti akka tumsu dhaamsi darbeera.
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://twitter.com/AbdiAminBaker/status/1709999548439900438?s=19

በሀገር ደኅንነት ላይ ሥጋት በሚፈጥር 
እና የውጭ ምንዛሪን በሚያሳጣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ 30 ግለሠቦችና የተለያዩ መሣሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ 

መስከረም 24 ቀን 2016  በአዲስ አበባ፣ ሸገር ከተማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ አዳማ፣ ሃዋሳ እና ጂማ ከተማ በተደረገ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ከ73 በላይ የቴሌኮም ማጭበርበሪያ ማሣሪያ እና 30 ተጠርጣሪ ግለሠቦች እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡ 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር በመተበበር እንዲሁም ከቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ባለሙያዎችና ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ላለፉት ሦስት ወራት በቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ተዋንያን ላይ ጥብቅና ምስጢራዊ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተቋማቱ ግኝቱን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን በላኩት የጋራ መገለጫ አመልክተዋል፡፡ 

ተጠርጣሪዎቹ የተለያዩ የግለሠብ ቤቶችንና ግቢዎችን በመከራየት የማጭበርበሪያ መሣሪያዎችን ተጠቅመው ወንጀሉን ሢሰሩ መቆየታቸውን ያስታወቀው መግለጫው፤ ለዚሁ ሕገ ወጥ ተግባር ሲውሉ የነበሩ ከ200 ሺ በላይ የሳፋሪኮም እና ኢትዮቴሌኮም ሲም ካርዶች መያዛቸውን አመልክቷል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉ የማጭበርበሪያ ጌትዌይ መካከልም በአንድ ጊዜ 127 የኢትዮቴሌኮም ወይም ሳፋሪኮም ሲም ካርድ መያዝ የሚችል መሣሪያ መገኘቱንም ጠቁሟል፡፡ 

በእነዚህ መሣሪያዎች አማካኝነት የሚፈጸሙት የማጭበርበር ድርጊቶች ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሪ እንደሚያሳጣ የጠቆመው መግለጫው፤ ኢትዮቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከ500 ሚልዮን በላይ ብር በዚህ ሕገ ወጥ ተግባር የተነሳ ማጣቱን አስታውቋል፡፡
 
ሕገ ወጥ ድርጊቱ በሀገር ደኅንነት ላይ ሥጋት የሚፈጥርም መሆኑን ያመለከተው የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጋራ መግለጫ፤ በማጭበርበሪያ መሣሪያዎች የተነሳ በቴሌኮም አገልግሎት አሰጣጥ ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ጠቁሟል፡፡
 
መሣሪያዎቹ በሕገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሲሆን፤ ከኢትዮቴሌኮም ይሁን ከሳፋሪኮም ምንም እውቅና የሌላቸው ነገር ግን ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎችን ኢትዮ ቴሌኮም ወይም ሳፋሪኮም በዘረጋው ኔትወርክ ሳይሆን ራሳቸው በዘረጉት የማጭበርበሪያ ጌትዌይ ለደንበኞች የሚያቀርቡ መሆናቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡ 

በማጭበርበሪያ መሣሪያው የሚፈጸመው ሕገወጥ ድርጊት ሀገራዊ ጥቅምን ከማሳጣትና የደኅንነት ሥጋት ከመደቀን ባሻገር የቴሌኮም ደንበኞች በሚፈጠረው የትራፊክ መጨናነቅ ጥራት ያለው የኔትዎርክ አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረጉን፤ በዚህም ደንበኞች በቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም በመንግሥት እንዲማረሩና ሀገራዊ መረጋጋት እንዳይኖር አስተዋጽዖ ማበርከቱን መግለጫው አስታውቋል፡፡  
በማጭበርበር ወንጀሉ ላይ የሚሳተፉ ግለሠቦች ሰፊ ኔትዎርክ ያላቸው ሲሆን፤ ከአለም ዓቀፍ ተዋንያን እስከ ሀገር ውስጥ ቤት አከራይ ድረስ ትስስር መፍጠራቸውን የተቋማቱ የጋራ መግለጫ አስታውቋል፡፡  

የማጭበርበሪያ መሣሪያ ከጎረቤት ሀገራት በድንበር በኩል እስከ መሀል ከተማ ድረስ የሚቀባበሉ ደላሎች፣ በርካታ የኢትዮቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ሲም ካርድ እና ሞባይል ካርድ ለእነዚህ አጭበርባሪዎች የሚያደርሱ ተባባሪ ወንጀለኞች እንደሚገኙበት አመልክቷል፡፡ በተለይ ተጠርጣሪዎች መቀመጫቸውን ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ሌሎች ሀገራት ካደረጉ ዜጎች ጋር በመመሳጠር እና ተቀጥረው በመሥራት ተሳትፎ ሲያደርጉ እንደተደረሰባቸው ጠቁሟል። 

እንደ ኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጋራ መግለጫ፤ በኦፕሬሽኑ በተያዙት መሣሪያዎች እና በተጠርጣሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቀጣይ ምርመራውን አጠናክሮ በመቀጠል፤ በቀጣይ ለሕዝብ የማሳወቅ ሥራ የሚያከናውን ይሆናል፡፡ ሁሉም አካላት በሀገር፣ በዜጎች እና በተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱት እነዚህና ሌሎችም መሰል ወንጀሎች ከጸጥታ እና ደኅንነት ተቋማት እይታ እንደማይሰወሩ ተገንዝበው ከሕገወጥ እንቅስቃሴዎች ሊቆጠቡ ይገባል ብሏል መግለጫው።
  
ኅብረተሰቡም የቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊቶች ከሚያደርሱት የኢኮኖሚ ኪሳራ በተጨማሪ በሀገር ደኅንነት ላይ የሚያስከትሉትን አደጋ በመገንዘብ በተመሳሳይ ወንጀል የሚሳተፉ ግለሠቦችና ተቋማት መኖራቸውን ጥርጣሬ ሲያድርበት በአካባቢው ለሚገኙ የጸጥታና የሕግ አስከባሪ አካላት ጥቆማውን በመስጠት ሕገ-ወጦችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽዖ አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመግለጫቸው አሳስበዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

SEENA ARTIST HALLOO DAWWEE

R. I. P🙏 Artist Halloo Dawwee

Biiroon Eegumsa Fayyaa Oromiyaa, Irreechaf Dhamsa Dabarsaniiruu...